AddisLidet 2017 | Page 16

በጊዜው በጣም አስፈላጊና ወደ ጎን የማይባሉ ስለሚመስሉን ጉልበታችንን ይመጡታል ፡፡ ክርስቲያን ፋታ ወስዶ መንፈሳዊ ሁኔታውን በመፈተሸ ፣ የሥራ ኀላፊነት ለመቀበል እንዳይችል ሆኖ በሥራ ከተጠመደ ፣ ለአስቸኳዩ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ሎሌ ያድራል ፡፡ በራሱና በሌሎች ዐይን ዋጋ የሚሰጠው የሚመስል ነገር ፣ ሌት ተቀን ሠርቶ ማከናወን ቢችልም ፣ እግዚአብሔር ያቀደለትን ሥራ ግን ሳያጠናቅቅ ይቀራል
እንግዲያው በባርነት ቀፍድዶ የያዘን “ አስቸኳይ ” የሚባል አምባ ገነን የፍዳችን አንዱ ዋና ምክንያት መሆኑ ነው ፡፡ አስቸኳዩን ከዋናው ጉዳይ እንዴት እንለያለን ? የሚለው ጥያቄ ብርቱ ጥያቄ ነው ፡፡ ለዚህ መልስ ካገኘን የፍልሚያው እምብርት ታወቀ ማለት ነው ፡፡ የቢዚነት ጉዳይ ግን ከዓላማ አንጻር ብቻ ሳይሆን በጊዜ አስተዳደር አንጻርም ሊታይ ይገባል ፡፡ ጊዜ ከፈጣሪ የተሰጠን ሀብት ነው ፡፡ ጊዜ ሀብት ከሆነ እንግዲያው እያንዳንዳችን “ መጋቤ ጊዜያት ” ሆነን በዚህ ሀብት ላይ ተሹመናል ፡፡ የጊዜ መጋቢነት እንዴት ይከወን ስንል ባለ ሙያዎች ከሚመክሩን መካከል ሦስቱን ብቻ ልጥቀስ ፡ - ጊዜዬ የት ጠፋ ? ምን አደረግሁት ? እያልክ የምትጠይቅ
ከሆነ ሥራዬ ብለህ የዕለት ዕለት እንቅስቃሴህን ለተከታታይ ሰባት ቀናት ያደረግከውን ነገር ስም እየሰጠህ ልትጽፈው ትችላለህ ፡፡ ከሳምንቱ በኋላ የጊዜ አጠቃቀምህን በዐይነቱ ስትሰድረው ጊዜህ ምን ላይ እንደዋለ የጊዜ ምጋቤ ባህርይህን ትረዳዋለህ ፡፡ ያኔ ያላግባብ የባከነ ወይም በቂ ጊዜ ያልተሰጠው ምን እንደሆነ ግልጽ ይሆናል ፡፡ ወገኖቼ ጤናችን እስኪዛባ ደስታችን እስኪጠፋ ቢዚ ከሆንን እየቆየ ወደ ክስመት ( burn out ) ልንሄድ እንችላለን ፡፡ በእምነት እጦት ሰበብ ሩጫ ያበዙትን ሕዝበ እስራኤል እግዚአብሔር እንደገሰጻቸውና እንደመከራቸው እኛንም ያስጠነቅቀናል ፡፡
ንጉሴ ቡልቻ
ከቤተክርስቲያኗ የፎቶ ማህደር
16