AddisLidet 2017 - Page 13

ለፍሬማነታችን 3 መሰረቶች
1 . በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል መመስረት ፍሬ ማፍራት ትልቅ ተስፋ ነው ። እግዚአብሔር በየጊዜው ለሕዝቡ የሚገባው ተስፋ ለፍሬያማነታችን መሠረት ነው ። እግዚአብሔር የእንደገና ዕድል የሚሰጥ አምላክ መሆኑ ይበልጥ ለፍሬያማነት አቅም ሰጭ አበረታች ጉልበት ነው ። በነብዩ ኢሳያስ እግዚአብሔር እስራኤልን ታፈራላችሁ ፣ ትበዛላችሁ እንዳለ ሁሉ እኛም አምላክ እናፈራ ዘንድ በሕይወታችን መከናወን ያለባቸውን የማፍራት ሂደቶችንም ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም ። ስለዚህ “ በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል ፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል ፤ በፍሬያቸውም ዓለሙን ፊት ይሞላሉ ።” ኢሳ27:6 ብሎ ሲናገር የተስፋ አምላክ የሆነ እግዚአብሔር ፍሬአማ እንድንሆን የሚፈልግና ደግሞም ቃሉን ጠብቆ የሚኖር ታማኝ አምላክ መሆኑን ማመን ያስፈልጋል ።
2 . የምንዘራበትንና የምናጭድበትን ወቅት መለየትና መጠበቅ በመዝራትና በማጨድ መርህ ሂደት አንዱ ወቅትን ማወቅና መጠበቅ ነው ። ብዙ ምርታማ የሆነ ገበሬ ዘሩን ሲዘራም ሆነ አዝመራውን ሲያጭድ ከሚያደርጋቸው ዋና ነገሮች አንዱ ወቅቱን ጠንቅቆ በማወቅና በመጠበቅ አስፈላጊውን ዝግጅትና እንክብካቤ ማድረግ ነው ። ስለዚህ ከፍሬ እርቃ ጠውልጋና ደርቃ ለነበረች እስራኤል እንደገና የማፍራት ዜና ሲያበስራት የማፍሪያዋን ወቅት “ በሚመጣው ዘመን ...” በማለት አስቀድሞ በመናገር ነበር ። ዛሬ በብዙ ድርቀትና መካንነት እያለፍን ላለን ደክመን ከምናገኛቸው ውጤት ጋር አልጣጣም ላለን ወገኖች ትልቅ የምስራች አለኝ ! አሁን ቆማችሁ ባለመከናወናችሁ የምታዝኑበት ዓመት ሳይሆን ታፈሩና ትከናወኑ ዘንድ የተነገረላችሁ ወቅቱን በማወቅ ዘመናቹሁን የምትዋጁበት የዘር ጊዜ መሆኑን መገንዘብ የግድ ይለናል ። የእስራኤል ትልቁ ችግሯ የመጎብኛዋን ወቅት አለማወቋ ነበር ። በሯ ድረስ ከመጣው አዳኝ ጋር የተላለፈችው ለትምህርት ሆኖን ዛሬም የኛን ጉብኝት
አንዳናሳልፍ ንቁ ልንሆን ይገባል ።
3 . የፍሬያማነትን ሂደት ዑደቱን ጠብቆ መኖር ሥር መሥደድ ፣ ማበብ ፣ መጨብጨብ ፣ ማፍራትና ማካፈል የፍሬያማ ሕይወት ዑደቱን ጠብቆ መኖር መሰረታዊ መለኪያዎች ናቸው ፡፡ እነዚህን አምስት የፍሬያማነት መለኪያዎች ከዚህ በታች በጥቂቱ እንመለከታለን ፡፡
ሀ ) ሥር መሥደድ ፦ ፍሬያማነት በበቀለው ዛፍ ባለው ሥር መስደድ ይወሰናል ። የማይታየው የቤት መሠረት ውጭ ለሚታዩት ወለል ፣ ግድግዳና ጣራያ መቆም ምክንያት እንደሆነ ሁሉ እንዲሁ ሥር መስደድ ነገ በአደባባይ ለሚገለጠውና ለምናፈራው ፍሬ ቀድመን በስውርና በትኩረት የምንሠራው ተግባር ነው ። ጥብቅ ወደ ሆነ መንፈሳዊ ወቅት እየገባን እንደሆነ እረዳለሁ ስለሆነም የሚመጣው መንፈሳዊ ጉብኝት እንዳያልፈንም ሆነ እንዳያጠፋን ሥር ሰደን መመሥረት የግድ ይለናል ።
ለ ) ማበብ ( blossom ):- ይህ ወቅት በስውር ሥር የሰደደው ቡቃያ ለማፍራት የሚዘጋጅበት ልዩ ወቅት ነው ። ወደ ታች ሥር መሥደድ ብቻ ሳይሆን ወደ ላይና ውጭ በሚታይ መልኩ ለፍሬ ተስፋ ሰጭ የሆነ የእድገት ደረጃ ነው ። እንዲህ ዓይነት ተስፋ ሰጭ ቃል ኪዳን ያለ ፍሬ ለብዙ አመታት ላስቆጠረች ለእስራኤል ከፍተኛ የሆነ ትርጉም ሰጭ ነበር ። በሕይወት ማበብ የማፍራት ሂደት የእድገት ደረጃ እንጂ የመጨረሻው ውጤት አይደለምና ወቅቱን ጠብቆ ወደሚቀጥለው የእድገት ደረጃ እንዲያድግ እድል መስጠትና በትዕግስት የበኩላችንን ጥረት ልናደርግ ይገባል ።
ሐ ) መጨብጨብ ፦ መጨብጨብ የሥር መስደድ ወራትን ተከትሎ ከማበብ በኋላ የሚመጣ የማፍራት ሂደት ነው ። በምድረ በዳ በጥም ለተንገላታች ዘርታ ማጨድ ተስኗት ለነበረች እስራኤል የማፍሪያውን ...
ይቅጥላል ...
13