AddisLidet 2017 | Page 12

ፍሬያማነት !
በመጋቢ መካሻው ሺመላሽ

ፍሬያማነት !

የንባብ ክፍል ፦ “ በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል ፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል ፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ ።” ኢሳ27:6
መግቢያ
የሠው ልጆችን ሁሉ የሚያመሳስሏቸው የተለያዩ ፍላጎቶች አሉ ። ለምሳሌ ያላገባ ማግባት ፣ ያገባ ጸንሶ መውለድ ፣ ገበሬው ዘርቶ ማጨድ ፣ ተማሪው ተምሮ መመረቅ ፣ ነጋዴው ነግዶ ማትረፍና ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚሉ ማቆሚያ የሌላቸው ፍላጎቶች የሚጠቀሱ ናቸው ። እነዚህን ነገሮች መፈለጉና ለማግኘት ጥረት ማድረጉ ክፋት የሌላውና ቅቡል ቢሆንም እነዚህ ማብቂያ የሌላቸው የሰው ፍላጎቶች በራሳቸው ግብ አለመሆናቸውንና ወደ ዋናው ግባችን በምናደርገው ጉዞ ላይ አስፈላጊና አጋዥ የሆኑ ግባቶች ናቸው ። ሕይወታችን ፍሬያማ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔርም ሆነ የሰው ልጆች ብርቱ ፍላጎት ነው ። ይህን የፍሬያማነት ሕይወት አምላክም ሆነ ሰው በጋራ ይጠብቁብናል ።
ፍሬ ለማፍራትም ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ ጥረትም ይጠይቃል ። ስለዚህ ጣፋጭና የተትረፈረፈ ፍሬ ማፍራት መፈለግ መብት ብቻ ሳይሆን ለእውነተኛ ደቀ መዝሙር ግዴታችም ጭምር መሆኑን በማጤን ይበልጥ ለፍሬያማነት እንድንቀሳቀስ ይገባል ። እንደተሰጠንና ፍሬ ለማፍራት ጥረት እንዳደርግን መጠን ፍሬ እናፈራ ዘንድ መልካም ዘርን የዘራብን አምላክ ከእያንዳንዳችን ፍሬ ይጠብቅብናል ። ከላይ የተጠቀሰው ኢሳ27:6 ክፍል
ለእስራኤል ሕዝብ እንደገና እድል የሚሰጣቸው እስራኤል ከዚህ በፊት ብዙ ተደክሞባት የተጠበቀባትን ፍሬ ማፍራት አለመቻሏ ነበር ። አሁን ግን ታሪካዊ ስህተት እንዳትደግም መልካምን ፍሬ እንድታፈራ ይጠበቅባትል ። ስለ ፍሬ ማፍራት ስናወራ ልብ ማለት ያለብን ነገር የፍሬያችን ዓይነት ሊለያይ ይችላል እንጂ ሰው የዘራውን በሕይወቱ መብቀሉና ማጨዱ አይቀሬ ነው ። የሰው ሕይወት በመዝራትና ማጨድ ህግ ( መርህ ) ላይ የተመሠረተ ነው ። ይህ የመዝራትና የማጨድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሰው የሚሠራ ዓለም አቀፋዊ መርህ ነው ። ስለዚህ ወደድንም ጠላንም የዘራነውን ጊዜ ጠብቀን እንደዘራነው የዘር ዓይነት እናጭዳለን ። ጥያቄው ምን ዘርተን ምን አጨድን ? ነው :: መልሱ ደግሞ ቆም ብለን ቤታችን እየተከታተሉ የገቡትን ውጤቶች መመልከት በቂ ማስረጃዎች ናቸው ። ስለዚህ በስጋ ዘርተን መበስበስን እንዳናጭድ ከመንፈስ ዘርተን የዘላለምን ሕይወትና የምድርን በረከት ማጨድ እንድንችል እግዚአብሔር እንደገና ለማፍራት አስቀድመን ስር የምንሰድበትን ዘመን በፊታችን አምጥቷልናል ።
ይቅጥላል ...
12