AddisLidet 2017 | Page 11

ጉራማይሌ

ጉራማይሌ

ጉራማይሌ ምርኩዝ ሽልምልሜ በትር ቢደክም አያሳርፍ ከአዳኝ አውሬ አይበግር ቅጥልጥል ድብልቅልቅ የይሁን ባዘቶ አይሞቅ አይቀዘቅዝ በአንድነት ተሰፍቶ ማጌጥ ጀምረናል በዘመን ድሪቶ ማጌጥ ጀምረናል በዘመን ቡትቶ ማጌጥ ጀምረናል ማጌጥ ከተባለ በዝብርቅርቅ ነገር በተመሳቀለ ማዜም ጀምረናል ማዜም ከተባለ ከስጋ ከመንፈስ በተቀላቀለ መለየት ተስኖን ቆመዋል በአንድነት ዳጔን እና ታቦት ኪነት እና ክሕነት መለየት አቅቶን ቆመዋል በአንድነት ዝማሬ እና ዘፈን ኪነትና ክሕነት ።
ከካሌብ አብርሃ ( ቴዲ )
ከቤተክርስቲያኗ የፎቶ ማህደር
11