AddisLidet 2017 | Page 10

መጪውን አመት አዲስ ጅማሬን የምንጀምርበት ፣ አሐዱ ብለን አዝመራን የምናዘምርበት ፣ ጠፍ የሆነውን የልባችንን መሬት እንደገና የምናለሰልስበት ፣ የተዘራውን የምናርምበት ፣ ወደላይ ከመታየት ይልቅ ወደታች ስር የምንሰድበት ፣ መሰረት የምንጥልበት ፣ አገልግሎትና እውነተኛ ሕብረት የምንመሰርትበት ፣ ትምህርት የምንጀምርበት ፣ ትዳር የምንጀምርበት ፣ በገንዘባችን እየተጠቀምን ጌታን የምናገለግልበት ፣ ዘመን ጌታ ከፊታችን አምጥቶአል ፡፡ በዚህ የአዝመራ አመት ለታይታ የምንጠራራበት ሳይሆን በጉዋዳችን የምንተጋበት ፣ ይቅር የምንልበት ፣ ይቅርታ የምንቀበልበት ፣ ሐጢያትን እየተጠየፍን አንዳንዶችን ከእሳት ነጥቀን የምናወጣበት ፣
የጣልነውን እንቁ የምናነሳበት ፣ በተሰጠን መክሊት በትጋት የምንነግድበት ፣ ደካሞችን የምንረዳበት እንደገና የምናገለግልበት ዘመን መጥቶልናል ፡፡ በመጨረሻም ፤ ቤተሰቤን ፣ ባጠገቤ ያሉትን ወንድሞችና እሕቶቼን ፣ ቤተክርስቲያኔንና ጆሮውን ላዋሰኝ ወገኔ ሁሉ 2017 ዓ . ም መልካም ዘር የምንዘራበት ፣ በቂ ውሐ ለማግኘት ወደቃሉ ምንጭ የምንሔድበት ፣ መሰረታችንን የምናጸናበት ፣ ለልጆቻችንና ለቀጣዩ ትውልድ በረከት ለመሆን የምንተጋበት የአዝመራ አመት እንዲሆንልን ጸሎቴ ነው ፡፡
አዳም ቱሉ ( ዶ / ር )
ሙሾውን ይደርድር ! የሞት ፍርድ ይፈረድ ፣ በፍቅር ጎራዴ ጥላቻ ይታረድ ። ደግሞ እንዳይነሳ ፣ እንዳያንሰራራ ፣ በወሬ ዳሰሳ ፣ በሀሜት ነቀርሳ ፣ በክፋት ትንኮሳ ፣ በ ... ቃ ... አብረው ይቀበሩ ፣ እነቅናት ሁሉ ፣ ፍፁም እንዳይቀሩ ። ሙሾውን ይደርድር ሰይጣን ከነአበሩ ፣ ጥላቻ ከሞተ ሰላም ነው ሀገሩ ።
ከቤተክርስቲያኗ የፎቶ ማህደር
በሩት ( ቹቹ )
10